Home » Archives by category » የዕለቱ ዜናዎች
በኢትዮጵያ እና በአለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ መካከል የ90 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈረመ

በኢትዮጵያ እና በአለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ መካከል የ90 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈረመ

 በኢትዮጵያ መንግስትና በአለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ መካከል የ90 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት ተፈረሟል። ስምምነቱን በሮም የኢፌዴሪ ቋሚ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ዘነቡ ታደሰ እና የአለም አቀፍ የግብርና ልማት ፈንድ ፕሬዚዳንት ጊልበርት ሁንግቦ በዛሬው ዕለት ተፈራርመዋል። የብድር ስምምነቱ ለቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል መሆኑን በጣሊያን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። በረጅም ጊዜ የሚመለሰው […]

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው በደል መቆም እንዳለበት የአማራ ተማሪዎች ማኅበር ጠየቀ

የአማራ ተማሪዎች ማኅበር ዘርን መሠረት ያደረገ ጥቃት መቆም እንዳለበት የጠየቀው በባሕር ዳር ከተማ በተካሄደው ስብሰባው ነው። በተፈጠረው አለመረጋጋት ትምህርታቸውን ያቋረጡ፣ በባሕር ዳርና አካባቢው የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ተማሪዎች በውይይቱ ተሳትፈዋል። የአማራ ሕዝብ ልክ እንደሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች ሁሉ በሀገር ግንባታ ሂደቱ ጉልህ አስተዋፅኦ ያደረገ ሆኖ እያለ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ባሉ ልጆቹ ላይ ዘርን […]

Continue reading …
የሕብር ሬዲዮ ሕዳር 07 ቀን 2012 ዓ.ም. ፕሮግራም

ከኢህአዴግ ውህደት እስከ ህግ የማስከበር እና ስጋት ላይ የወደቀው የዜጎእች ደህንነት  (ያድምጡት) የጠቅላይ ሚኒስትሩ መንታ ገጽታ  (ልዩ ጥንቅር) ሌሎችም ዜናዎቻችን የሲያትሉ ጠንካራ ተቃውሞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በወቅቱ ችግር ተጠያቂ ናቸው መባሉ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ ኮሚሽን  የመዋቅር ለውጥ ያሻዋል ተባለ ታላቁ ሩጫ ዘንድሮም ብሶት መግለጫ ሆነ ኢትዮጵያ አየር መንገድ የደ/ሱዳን ተጓዦችን አስጠነቀቀ የሕወሓት ትግራይን እገነጥላሁ ማለት የሚጎዳው ትግራይን […]

Continue reading …
በቦሌ ኤርፖርት 12 ሚሊየን 64 ሺህ ብር የሚያወጣ አደገኛ አደንዛዥ ዕፅ በቁጥጥር ስር ዋለ

መነሻውን ከብራዚል ሳኦፖሎ ያደረገ አደገኛ አደንዛዥ ዕፅ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ ቁጥር ET 507 በቀን 07/03/2012 ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርስ በዓለም አቀፍ መንገኞች ማስተናገጃ ተርሚናል በጉምሩክ ኢንተሊጀንስ ሰራተኞችና በኢንተር ፖል አባል እንዲሁም በሰዓቱ ከነበረ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ሰራተኛ ትብብር በቁጥጥር ስር ውሏል። በሰዓቱም አደንዛዥ ዕፁን ሲያዘዋውር የነበረው ግለሰብ ባራቱንደ ሞጆድ የፓስፖርት ቁጥሩ […]

Continue reading …
ህዝባዊ ዉይይት በሀገራችን ኢትዮጵያ አንድነት እና በህዝቦቿ ላይ ያንዧበቡ አደጋዎችና፤ መንስኤዎቻቸው፤ እንዲሁም መፍትሄዎች ላይ ዋሽንግተን ዲሲ

ህዝባዊ ዉይይት በሀገራችን ኢትዮጵያ አንድነት እና በህዝቦቿ ላይ ያንዧበቡ አደጋዎችና፤ መንስኤዎቻቸው፤ እንዲሁም መፍትሄዎች ላይ ዋሽንግተን ዲሲ

Continue reading …
የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስለውሕደቱ አቅጣጫ ሊያስቀምጥ እንጅ ውሳኔ ሊያሳልፍ እንደማይችል አስተያዬት ሰጭዎች ገለጹ

የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ለመወያዬት ስብሰባ ተቀምጧል፤ ከዚህ ጋር በተያያዘ በርካቶች ስለውሕደቱ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ እየጠበቁ ነው፤ አንዳንዶች ደግሞ ስለውሕደቱ አቅጣጫ ሊያስቀምጥ እንደሚችል እንደሚገምቱና በውሕደቱ ዙሪያ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴውም ሆነ ማዕከላዊ ኮሚቴው የመወሰን ስልጣን እንደሌለው እየገለጹ ነው፡፡ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (አዴፓ) ምክር ቤት ሰብሳቢና የሕግ ባለሙያ አቶ ሐዲስ ሐረገወይን ለአብመድ በሰጡት […]

Continue reading …
በሲያትል ዋሽንግተን እና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በ አያቶላ ጀዋር እና ደጋፊዎቹ ላይ እየተደረገ ያለ የተቃውሞ ሰልፍ

በሲያትል ዋሽንግተን እና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በ አያቶላ ጀዋር እና ደጋፊዎቹ ላይ እየተደረገ ያለ የተቃውሞ ሰልፍ OMN:Marii Hawaasa Oromoo Seattle Jawaar Mohammed waliin (SAD 17,2019) OMN:Marii Hawaasa Oromoo Seattle Jawaar Mohammed waliin (SAD 17,2019) Posted by Oromia Media Network on Sunday, November 17, 2019

Continue reading …
‹‹የአማራና የትግራይ ሕዝቦች በጋራ እሴቶቻቸው የተጋመዱ፤ የተንሻፈፈ ፖለቲካ የማያቆራርጣቸው ናቸው፡፡›› በጎንደር የትግራይ ተወላጆች

‹‹ጎንደር ከትግራውያን ጋር የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማድረግ ዝግጁ ናት፡፡›› የጎንደር ከተማ አስተዳድር አዴፓ ጽሕፈት ቤት በ1957 ዓ.ም ነበር ፍቅር ጎንደር ላይ እንዲከትሙ ያደረጋቸው። ያኔ ውኃ አጣጫቸውን አግኝተው አስር ልጆችን አፍርተዋል። ባለታሪካችን ትውልዳቸው ትግራይ ክልል ኑሯቸው ጎንደር ነው፤ አቶ ወልደገብርኤል ትኩ ይባላሉ፡፡ ዋልታና ማገሯ ጎንደር ያለ ልዩነት አኑራቸዋለች። “ጎንደር ውስጥ ከሰውነት ቀጥሎ ብሔር ብርቅየየ አንድነትን መፍጠሪያ […]

Continue reading …
አንጋፋው ጋዜጠኛና ዲፕሎማት አሀዱ ሳቡሬ በተወለዱ በ 94 አመታቸው ከቤተዘመዶቻቸው ጋር ይኖሩበት በነበረው ሎስ አንጀለስ ከተማ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል

ዜና እረፍት ! አሐዱ ሳቡሬ ፣ አጠገበኝ ወሬ !!! የሀገር ባለውለታ፤የሐገር አድባር ዜና እረፍት አንጋፋው ጋዜጠኛና ዲፕሎማት አሀዱ ሳቡሬ በተወለዱ በ 94 አመታቸው ከቤተዘመዶቻቸው ጋር ይኖሩበት በነበረው ሎስ አንጀለስ ከተማ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። ጋዜጠኛ አሀዱ በዘመነ ጃንሆይ ” አሀዱ ሳቡሬ አጠገበኝ ወሬ ” የተባለላቸው ድንቅ ጋዜጠኛ እንደነበሩ መገናኛ ብዙሃን ዘግበውላቸዋል። ፈጣሪ የአምባሳደር አሀዱን ነፍስ […]

Continue reading …
‘‘አገር የግል እና የተወሰኑ ቡድኖች መጠቀሚያ አይደለችም’’ – የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም

አዲስ አበባ፡- “አገር የግል እና የተወሰኑ ቡድኖች መጠቀሚያ አይደለችም። ስለዚህ ሁሉም በጋራ የኢትዮጵያን አንድነት ሊጠብቅ ይገባል” ሲሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም ጥሪ አቀረቡ፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ትናንት በፍሬንድ ሺፕ ሆቴል ባዘጋጀው የህዝብ ለህዝብ መድረክ ላይ አፈጉባኤዋ ወይዘሮ ኬሪያ እንደተናገሩት፤ በግለሰቦች እና በተወሰኑ ቡድኖች ምክንያት በተለይ ባለፉት ሁለት እና ሦስት ዓመታት ውስጥ […]

Continue reading …
የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤትን ወይም የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤትን በመጥቀስ የገንዘብ እና የልዩ ልዩ ድጋፍ ጥያቄ ቢቀርብላችሁ ትክክለኝነቱ የተረጋገጠ የጽ/ቤቶቹ የድጋፍ ደብዳቤ በአባሪነት መያያዙን ማረጋገጥ አለበውት

አንዳንድ አካላት ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት እውቅና ውጪ፣ አብረን እየሰራን እንገኛለን በማለት የጽሕፈት ቤቱን ስም በመጠቀም ለተባባሪና አጋር አካላት የገንዘብ እና የልዩ ልዩ ድጋፍ ጥያቄዎችን ሲያቀርቡ ተስተውሏል። ስለሆነም፣ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤትን ወይም የቀዳማዊት እመቤት ጽሕፈት ቤትን በመጥቀስ የገንዘብ እና የልዩ ልዩ ድጋፍ ጥያቄ ቢቀርብላችሁ ትክክለኝነቱ የተረጋገጠ የጽ/ቤቶቹ የድጋፍ ደብዳቤ በአባሪነት መያያዙን ማረጋገጥ፣ በተጨማሪም ወደ […]

Continue reading …
” ዛሬ የፓርቲ ዉሕደቱን በተመለከተ ያደረግነዉ ወሳኝ ስብሰሰባ አመርቂ ዉጤት አስመዝግቧል” – ጠ/ ሚኒስትር አብይ አህመድ

” ዛሬ የፓርቲ ዉሕደቱን በተመለከተ ያደረግነዉ ወሳኝ ስብሰሰባ አመርቂ ዉጤት አስመዝግቧል:: ዉሕደቱ የኢትዮጵያን የፌዴራል ሥርዓት ይበልጥ የሚያጠናክር፣ ተሰሚነት ላልነበራቸዉ አጋር ድርጅቶች እኩል ድምጽ የሚሰጥ ኅብረ ብሔራዊነትን የሚያጸና፣ አካታችነትንና ፍትሐዊ ዉክልናን የሚያረጋግጥ ሁነኛ አቅጣጫ ነዉ:: የፓርቲው ውሕደት ሀገራዊ አንድነትን ከኅብረ ብሔራዊነት ጋር አስተሣሥሮ ለመጓዝ ዕድል የሚሰጥ ነው ” ( ጠ/ ሚኒስትር አብይ አህመድ )

Continue reading …
ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን በመጠቀም ሀሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን ሲያትሙ የነበሩ የውጪ ሀገር ዜጎችን በቁጥጥር ስር ዋሉ

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት እና የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በቅንጅት ባደረጉት ክትትል ልዩ ልዩ መሳሪያዎችን በመጠቀም ሀሰተኛ የገንዘብ ኖቶችን ሲያትሙ የነበሩ የውጪ ሀገር ዜጎችን በቁጥጥር ስር አዋሉ፡፡ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ያደረገውን ክትትል ተከትሎ ስምንት የውጪ ሀገር ዜጎች በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ሜታ ፋብሪካ አካባቢ ሁለት መኖሪያ ቤቶችን በመከራዬት በሕገ-ወጥ መንገድ ሀሰተኛ […]

Continue reading …
የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ በአብላጫ ድምጽ ውህደቱን አጸደቀ ሕወሓት ተቃወመ

የኢህአዴግ ውህደት በሦስቱ አባል ድርጅቶች ድጋፍና በህወሓት #ተቃውሞ ፀድቋል‼የኢህአዴግ ውህደት የፀደቀው በ27 ድጋፍ ፣ በ6 ተቃውሞ ነው። ይሁን እንጂ ህወሓት ውህደቱን ሙሉ ለሙሉ አልተቃወመም። ከዚያ ይልቅ ውህደቱን አስመልክቶ #ከማዕከላዊ ኮሚቴ ጋር ተመካክሮ እንደሚወስን በመግለፅ ተጨማሪ ቀናት እንዲሰጡት ጠይቋል። በዚህ መሠረት የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ለህወሓት የ3 ቀናት ግዜ ገደብ ሰጥቶታል። በውህደቱ ላይ የተስማሙት አባልና አጋር ድርጅቶች ግን ከነገ ጀምሮ በአዲሱ ፓርቲ ፕሮግራም ላይ መወያየት ይጀምራሉ […]

Continue reading …
ፖለቲከኞች የራሳቸውን ስራ ይስሩ፤ ከዚያ ውጪ ያለን ሰዎችም የየራሳችንን ሥራ እንስራ፤ ይህ ሲሆን ሁሉም ይስተካከላል – ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት

• የትም አገር ለውጥ ቀላል ሆኖ አያውቅም፡፡ የተለያየ የቡድን ፍላጎት ይኖራል፡፡ ወደፊት ወደኋላ የሚያስኬዱ ሁኔታዎችም አሉ፡፡ • አሁን ላይ አፌን ሞልቼ መናገር እችላለሁ። ምንም አይነት የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት የለም፡፡ ዳኞች እንዲያውም አሁን “ነፃ ሆነን ህጉን ተከትለን እየሰራን ነው” በማለት ላይ ይገኛሉ፡፡ • ማንኛውም ህዝብ በሰላም ወጥቶ ለመግባት ሥርዓት ኖሮ በህግ መተዳደር ይፈልጋል። ነገር ግን፤ አንዳንዴ […]

Continue reading …
ለጤናወ ግድ ይለወታልን? እንግዲያስ  ይቺን ያንብቡ!

ጤና ይስጥልኝ! ለጤናወ ግድ ይልወታልን? እንግዲያስ  mahderetena.com   ይጎብኙ በኢትዮጵያዉያን ዘንድ የተለየ፣ በሌሎች አገሮች ብዙ የማይታይ  ሰላምታ አሰጣጥ አለ። ሰዎች ሲገናኙ ብቻ ሳይሆን ሲለያዩም ይጠቀሙበታል።  «ጤና ይስጥልኝ»  የሚለው ሰላምታ። ጤና ክቡር ነው። ጤና ተፈላጊ ነው። ጤነኛ መሆን የሁሉም ሰው ምኞት ነው። ጤነኛ መሆን መታደል ነው። አንድ ሃብታም ሴት ነበሩ። ድረደዋ። የስኳር በሽታ በጣም አጠቃቸው። ከዚህ አለም […]

Continue reading …
ዩኒቨርሲቲዎች ወደ መረጋጋት የማይገቡ ከሆነ እስከ መዝጋት የሚደርስ እርምጃ እንደሚወሰድ ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጠነቀቁ፡

በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ረብሻ በመፍጠር የሰው ሕይወት እንዲያልፍ በሚያደርጉ ተማሪዎች ላይ መንግሥት ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶክተር) ገለፁ፡፡ ረብሻ በመፍጠር የማይረጋጉ ዩኒቨርሲቲዎችን እስከመዝጋት የሚደርስ እርምጃ መንግሥት ሊወስድ እንደሚችልም ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጠንቅቀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ እየተፈጠሩ የሚገኙ ችግሮችን ለመፍታት ያለመ ውይይት ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የቦርድ ሰብሳቢዎች፤ ፕሬዝዳንቶች እና የክልሎች ሠላም እና […]

Continue reading …
በአማራና ኦሮሞ ህዝቦች ስም ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ ሰባት ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደረሱ

በአማራና ኦሮሞ ህዝቦች ስም ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱ ሰባት ፓርቲዎች በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን አስታወቁ፡፡ ፓርቲዎቹም የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ( አዴፓ) የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ( ኦዲፒ) የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ( ኦነግ)፣ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ( ኦፌኮ) ፣ የኦሮሚያ ብሄራዊ ፓርቲ (ኦብፓ) እና የአማራ ማህበራዊ ራዕይ ግንባር ናቸው፡፡ በሁለቱ ክልሎች እና ዩኒቨርሲቲዎች […]

Continue reading …
ዶ/ር በዛብህ ደምሴና ኢዜማ ተዋህደናል ማለታቸውን አስመልክቶ ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) መጋቢት 28/29 2011 ዓ.ም ባደረገው ጠቅላላ ጉባኤ 459 አባላት በተገኙበት 8ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄዱ ይታወሳል፡፡ በመሆኑም በዕለቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተወካይ በተገኙበት የስብሰባው ኮርም መሙላቱ ተረጋግጦ ጠቅላላ ጉባኤ ያለፈባቸውን ሂደት ገምግሞ ሲያበቃ በመኢአድ ውስጥ ወያኔ/ህወሓት አስቀምጧቸው የነበሩትን ዶ/ር በዛብህ ደምሴንና አቶ አበባው መሀሪን የጠቅላላ ጉባኤ አባላት ድምፅ በመንሳት ጉባኤው […]

Continue reading …
በኢትዮጵያ ህይወት ያለው ፍጡር ሊኖር የማይችልበት ቦታ መገኘቱ ተገለፀ

በኢትዮዽያ ዳሎል አካባቢ በፕላኔታችን ህይወት ያለው ፍጡር ሊኖርበት የማይችል ቦታ ማግኘታቸውን ሳይንቲስቶች አረጋገጡ ሲል ላይቭ ሳይንስ ድረ ገፅ ዘግቧል። የአፋር ዳሎል እሳተ ገሞራ አካባቢውን በማቃጠል ሞቃታማ የመሬት ገፅታ ፈጥሮ ጤናማ ባልሆነ የአረንጓዴ እና ቢጫ ቀለማት እንዲሞላ ማድረጉ አካባቢውን ህይወት ላለው ፍጡር አመቺ እንዳይሆን እንዳደረገው ነው ሳይንቲስቶቹ ያረጋገጡት። አዲሱን የጥናት ውጤት በግብዓትነት የተጠቀመው ዘገባው ሳይንቲስቶች አካባቢውን […]

Continue reading …
Page 1 of 546123Next ›Last »