Home » Archives by category » News Feature (Page 2)
የአዲስ አበባ ፖሊስ በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ስለመጠራቱ ጥያቄ ያቀረበልኝ አካል የለም አለ

በጀነራል ደግፌ በዲ የሚመራው የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ በአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ነገ እሁድ የካቲት 17/2011 ዓ/ም በመስቀል አደባባይ ሠላማዊ ሰልፍ ተጠርቷል በሚል በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች የተላለፈው ዘገባ ሀሰተኛ ነው ሲል መግለጫ ሰጠ:: “የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በነገው ዕለት ምንም ዓይነት የሠላማዊ ሰልፍ ሆነ ስብሰባ እናድርግ የሚል ጥያቄ አልቀረበልኝም ያለው” ኮሚሽኑ ሰልፉ የሚደረግ ከሆነ […]

Continue reading …
የትግራይ ክልላዊ መንግሥት ኢትዮጵያንና ኤርትራን የሚያገናኘውን የሁመራ ኦምሃጀር መንገድ ዘጋ

በሁመራ ኦምሀጁር በኩል ያለው የንግድ እንቅስቃሴ መዘጋቱ ተነገረ፡፡ ኤርትሪያን ፕሬስ ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው መንገዱን በአጣና የዘጋው የትግይ ክልል መንግስት ነው፡፡ ይህ የሁመራና ኦምሀጁር መንገድ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያና ኤርትራን የሚያገናኝ ዋናው መስመር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ በሁመራ ያሉ አንድ ምንጭ ለኤርትሪያን ፕሬስ እንደተናገሩት በዚያ መንገድ ሲጓዙ ከነበሩትና የኮንስትራክሽን መሳሪያዎችንና ጤፍ ጭነው የነበሩትን ከባድ መኪናዎች በማስቆም ትግርኛ ተናጋሪ ካልሆኑት […]

Continue reading …
በለገጣፎ ጉዳይ የኦሮምያ ክልል ፕረዚዳንት ለማ መገርሳ አቅጣጫ አስቀመጡ

በለገጣፎ የተወሰደውን እርምጃ ተከትሎ በአፈጻጸሙ ሂደት የተፈጠሩ ግድፈቶች እና ስህተቶች ካሉ ለይቶ ማረም አስፈላጊ መሆኑን በመግለጽ ይህንን ጉዳይ የሚያጣራ አንድ ግብረ ሀይልም ተደራጅቶ ወደ አካባቢዉ እንዲሰማራ የኦሮምያ ክልል ፕረዚዳንት ለማ መገርሳ አቅጣጫ ማስቀመጣቸውን አቶ አዲሱ አረጋ ገልጸዋል:: ግብረ ሃይሉም በጥቂት ቀናት ዉስጥ ወደማጣራት ስራ የሚገባ እና አጣርቶ በሚያቀርበዉ ሪፖርት መሰረትም ህገወጥ ግንባታን በማፍረስ ሂደት የተፈጸሙ […]

Continue reading …
አዲሱ አረጋ ከለገጣፎ  መልስ የጻፉት ጽሁፍ

በለገጣፎ ለገዳዲ ህገወጥ ናቸው በሚል እየተፈጸመ ያለው የድሃ ወገኖቻችንን መኖሪያ ቤቶች በተመለከተ ላለፉት ቀናት በስፋት እየዘገብን ይገኛል:: ሌሎች በርካታ ሚዲያዎችም ትኩረት ሰጥተው እየሰሩበት ይገኛሉ:: አብዛኛው ዘገባ እያተኮረ ያለው የወገኖቻችን ስቃይ መመልከቱና ማየቱ ላይ እንጂ መፍትሄው ምንድን ነው? እነዚህ ወገኖች ቀጣይ እጣ ፈንታ ምን ይሆናል? መንግስት ካለቤት የቀሩትን ወገኖች ምን ሊያደርጋቸው ነው? የሚሉ ጉዳዮች ትኩረት አልተሰጠባቸውም::’ […]

Continue reading …
‹‹ትላንት በመቀሌ አደባባዮች ሲሰድቡኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ወድጄዋለሁ፡፡ ዲሞክራሲ ነው፡፡›› ዶ/ር አብይ አህመድ

የፋይናንሺያል ታይምስ ጋዜጣ ዘጋቢዎቹ ዴቪድ ፒሊንግ እና ሊዮኔል ባርበር በአዲስ አበባ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮንና ቤተመንግስቱን እንደጎበኙ በዛሬ ዘገባቸው ጠቅሰዋል፡፡ በ40 ሺህ ሄክታር ላይ ባረፈው በዚህ ቤተመንግስት ከውጭ ጋዜጠኞች ጋር ዶ/ር አብይ አህመድ ለመጀመሪያ ጊዜ የአንድ ለአንድ ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡፡ በቃለምልልሱ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣን በተረከቡ የመጀመሪያው ቀን ፅህፈት ቤታቸው እንዲታደስ ትእዛዝ እንደሰጡ ተናግረዋል፡፡ በዚህ መሰረትም በሁለት […]

Continue reading …
አቶ ኤርሚያስ አመልጋ ለፍርድ ቤት ያቀረቡት አቤቱታ ተቀባይነት አገኘ

በቅርቡ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር የዋሉትና ክስ የተመሰረተባቸው አቶ ኤርሚያስ አመልጋ በማረሚያ ቤት ቆይታቸው ይሟሉልኝ በማለት ለፍርድ ቤቱ ያመለከቷቸው አቤቱታዎች ነበሩ። ከነዚህ መካከል በቁጥጥር ስር ከመዋላቸው በፊት የጀመሯቸውን ስራዎች ከማረሚያ ቤቱ እየወጡ ለማከናወን የተወሰነ ጊዜ እንዲፈቀድላቸው፣ መጽሐፍትና መጽሔቶች ማረሚያ ቤት እንዲገቡላቸው መጠየቃቸው ይገኝበታል፡፡ ተከሳሹ የግል ኩባንያ የቦርድ ሰብሳቢና ስራ አስኪያጅ መሆናቸውን በመግለጽ፣ ትልልቅ አገራዊ […]

Continue reading …
የጉራጌ ህዝባዊ ንቅናቄ(ጉህን) በዛሬው እለት መግለጫ አውጥቷል

የጉራጌ ህዝባዊ ንቅናቄ(ጉህን) በዛሬው እለት መግለጫ አውጥቷል፡፡ በመግለጫው  በጉራጌ ዞን የሶዶ እና የሚቄ ማዕከል የወረዳ ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ መፈታቱን ያደነቀው ጉህን ‹‹የጉራጌን ህዝብ ጥያቄ በአግባቡ መመለስ የዴሞክራሲ ስርዓት ከማስፈን አንጻር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡›› ብሏል፡፡ ይሁን የመስቃን ማእከል ወረዳ ነዋሪዎችም ተመሳሳይ ጥያቄ እንዳላቸው ገልፆ ‹‹በተመሳሳይ መልኩ ሰላማዊ እና ህጋዊ በሆነ መልኩ ህዝባዊ መሠረት እንዲኖረው ተደርጎ በአፋጣኝ […]

Continue reading …
19 ኤርትራዊያን ኬንያ ውስጥ ታሰሩ

  በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር የተጠረጠሩት 19 ኤርትራዊያን በዛሬው እለት ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የኬንያ ጋዜጦች ዘገቡ፡፡ እንደመረጃው ከሆነ ተጠርጣሪዎቹ በፕራዶ መኪና የኬንያን ሞያሌ ከተማ ሊያቋርጡ ሲሉ የተያዙት ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡ ከኢትዮጵያ ተነስተው የኬንያን ድንበር ሲያቋርጡ የተያዙት እነዚህ ተጠርጣሪዎች ኢትዮጵያ ውስጥ ክስ ስለቀረበባቸው ጠፍተው እየሄዱ መሆኑን ገልፀው እቅዳቸውም ዩኔንኤችሲአር ጥገኝነት መጠየቅ እንደነበር ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል፡፡ ፍርድ […]

Continue reading …
የጎንደር ሕብረት ለጎንደር ተፈናቃዮች አንድ ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር መመደቡን አስታወቀ

  “በመሃልና በምዕራብ ጎንደር በተፈጠረው ቀውስ ምክንያት በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መፈናቀላቸው ሲዘገብ ሰንብቷል። ቀውሱ በመተማና አካባቢው ሲጀምር መንግሥት ፈጥኖ እርምጃ ባለመውሰዱ ልዩ ልዩ አጀንዳ ያላቸው ታጣቂ ሃይሎች ሁኔታውን በመጠቀም ቀውሱ እንዲባባስ ለማድረግ እድል አግኝተዋል። በዚህም ምክንያት ከመተማ እስከ ጎንደር እና ከጎንደር እስከ ትክል ደንጋይ ከዚያም አልፎ ወደ ሁመራ በሚወስደው መንገድ ሁሉ ችግሩ እንዲባባስ ሆኗል። […]

Continue reading …
“ዜጐችን ማፈናቀል በአስቸኳይ ይቁም!!” – የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ መግለጫ

በኦሮሚያ ክልል አዲስ አበባ ዙሪያ ልዩ ዞን የለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር በ01 እና 02 ቀበሌዎች፣ ጭላሎ፣ ወበሪ፣ ለገዳዲ ቄራ፣ ገዋሳ፣እና በከተማዋ ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ መኖሪያ ቤቶችን “ህገወጥ ግንባታዎች ናቸው፤ ለአረንጓዴ ልማት ይፈለጋሉ” በማለት ከየካቲት 12 ቀን 2011 ዓም ጀምሮ በሃይል በማፍረስ ላይ ይገኛል። የከተማዋ ከንቲባ ለመገናኛ ብዙሃን እንደገለፁትም በቀጣይም ከ12 ሺህ በላይ ቤቶችን […]

Continue reading …
በሐዋሳ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በለሊት ተጀመረ

(ዘ-ሐበሻ) በሐዋሳ ከተማ የሲዳማ ክልል እንሁን ጥያቄ ሕዝበ ውሳኔው ዘግይቷል በሚል የተጠእራው ሰላማዊ ሰልፍ ገና ሳይነጋ ከጠዋቱ ከ 11 ሰዓት ጀምሮ መካሄድ ጀመረ:: በዘመቻ መልክ የተጠየቀ ዘንድሯዊ ጥያቄ የለንም:: ሰማ ዕቶቻችን ምስክር ናቸው ለሕገ መንግስታዊ ጥያቄያችን ሕገመንግስታዊ መልስ እንሻለለን ሕገመንግስታዊ መብታችን ይከበር:: የሪፈረንደም ቀን ተቆርጦ ይነገረን ሕገመንግስቱ ለሰጠን መብት የግለሰቦች ይሁንታ አያስፈልግም የሲዳማ ሕዝብ መንግስትን […]

Continue reading …
እነሆ መሃከለኛው መንገድ !  አማራጭ የሽግግር ኣሳብ

ገለታው ዘለቀ ከተባበረችው አሜሪካ 2/19/19 መግቢያ ኢትዮጵያ ሽግግር ላይ በመሆኗ ዜጎቿ ተስፋን ሰንቀዋል:: ምንም እንኳን ስጋቶች በግራም በቀኝም የተደቀኑ ቢሆንም ነገር ግን የህዝቡ ተስፋ ሃያል ነው። በተጨባጭ እየተወሰዱ ያሉ የለውጥ ርምጃዎች ብዙዎችን አነቃቅተዋል። ታዲያ የከረምንበት ፖለቲካ ውጤትና ራቅ ካለ ዘመን ጀምሮ ሲንከባለል የመጣ ችግር አለና ይህን የማሰናከያ ድንጋይ ገለል ኣድርጎ ዴሞክራቲክ ኔሽን ለመሆን ስርዓታዊ ለውጦችን […]

Continue reading …
የአባገዳዎችን ጥሪ በመቀበል የኦነግ ታጣቂዎች ወደ ካምፕ እየገባ ነው

  በአባገዳዎች እና እርቅ ቴክኒክ ኮሚቴ ባደረጉለት የሰላም ጥሪ መሰረት ታጣቂ ሀይሉ ከትላንት ጀምሮ ወደ ተዘጋጀለት ካምፕ እየገባ ነው፡፡ ታጣቂ ሀይሉ በቤጊ፣ጊዳአያና፣ በቦ ገምቤል ፣ መንዲ እና ጊዳሚ ወረዳዎችም በህዝቡ እና በመንግስት አካላት አቀባበል እየተደረገለት ነው፡፡ ከምዕራብ ዞን ብቻ ከአስር ሺህ በላይ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ታጣቂዎች ወደ ተዘጋጀላቸው ካምፕ መመለሳቸውን ቀድሞ የቱለማ አባገዳ በየነ ሰንበቶ […]

Continue reading …
በረቀቀ መንገድ ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ 4 መትረዬስ ጠብመንጃ እና ከ46 ሺ በላይ ጥይት መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን አስታወቀ

የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ባደረገው ክትትል በተሽከርካሪ አካል ውስጥ በረቀቀ መንገድ ተደብቆ ወደ አዲስ አበባ የገባ 4 መትረዬስ ጠብመንጃ እና ከ46 ሺ በላይ ጥይት መያዙን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሸን አስታወቀ፡፡ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 2 አ/አ A 77608 በሆነ «አቶዝ» የቤት መኪና በባለሙያ በመፍታት ወደ አዲስ አበባ የገባ 4 መትረየስ ጠብመንጃዎች ጥር 28 ቀን 2011 ዓ/ም […]

Continue reading …
የህዳሴው ግድብ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ለቻይናዊያን ተሰጠ

ስራው የቆመውን የህዳሴ ግድብ ግንባታ ለማስቀጠል የኢትዮጵያ መንግስት ስራውን ሙሉ በሙሉ ለቻይናዊያን መስጠቱ ታወቀ፡፡ የግድቡን ግንባታ በተመለከተ ከሁለት የቻይና ኩባንያዎች ጋር ስምምነት ተፈፀመ፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል በትላንትናው እለት የተፈራረመው ስምምነት40 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ መሆኑን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡ ሲጂጂሲ CGGC የተባለው የቻይናው ኩባንያ ግድቡ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2020 ስራ እንዲጀምር የሚያስችሉ ግንባታዎችንና ሌሎች ስራዎችን እንደሚያከናውን ተገልጿል፡፡ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ […]

Continue reading …
በ1997 ዓ.ም. የተደረገውን ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ የተፈጠረው ፖለቲካዊ ቀውስና የህዝብ ጭፍጨፋ በባለሙያ ተጠንቶ በመፅሀፍ መልክ እንዲቀመጥ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀመረ

በ1997 ዓ.ም. የተደረገውን ሀገራዊ ምርጫ ተከትሎ የተፈጠረው ፖለቲካዊ ቀውስና የህዝብ ጭፍጨፋ በባለሙያ ተጠንቶ በመፅሀፍ መልክ እንዲቀመጥ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀመረ፡፡ በአዲስ አበባ ታትሞ የሚሰራጨው ሳምንታዊው በረራ ጋዜጣ በዛሬ እትሙ እንደዘገበው ይህንን ጉዳይ በተመለከተ አና ጎሜዝ የበኩላቸውን እገዛ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡ በምርጫ 97 የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን መሪ የነበሩት አና ጎሜዝ በወቅቱ የተፈፀመውን ጭፍጨፋ በተመለከተ እሳቸው ዘንድም […]

Continue reading …
‹‹ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቅርቡ ስምምነት ሊፈፅሙ ነው”

  በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑት አቶ ሬድዋን ሁሴን በእንግሊዘኛ ቋንቋ ለንባብ ለሚበቃው መንግስታዊው ‹‹ኢትዮጵያን ሄራልድ›› ጋዜጣ በሰጡት መግለጫ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በቅርቡ ስምምነት ሊፈፅሙ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ይህም በሁለቱ አገራት መሀከል ያለውን አዲስ ግንኑነት በህጋዊ ማእቀፍ ለማረጋገጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ በአገራቱ መሀከል የሚኖረውን የንግድ ልውውጥ በተመለከተ ሰፊ ውይይት መደረጉን የጠቀሱት አምባሳደር ሬድዋን በዚህ […]

Continue reading …
በለገጣፎ -ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ቤታቸው የፈረሰባቸው ወገኖች ጠቅላይ ሚኒስትሩንም ሆነ አቶ ለማ መገርሳን ማነጋገር አትችሉም ተባሉ

  የለገጣፎ -ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር አረንጓዴ ቦታዎችን፥ የወንዝ ዳርቻዎችን፥ ከፈቃድ ውጭ የተያዙ እና ካሳ ተከፍሎባቸው ግንባታ የተካሄደባቸው ናቸው ያላቸውን ቤቶች ዛሬም ለሁለተኛ ቀን ሲያፈርስ ዋለ:: ትናንት ቤታቸዉ የፈረሰባቸዉ ግለሰቦች ዛሬ ጠዋት ተሰባስበዉ ወደ ኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳን አቶ ለማ መገርሳ ቢሮ አቤቱታቸውን ለማቅረብ  ቢያመሩም እሳቸዉን ማናገር አትችሉም ተብለው ወደ ክልሉ መሬት አስተዳደር ቢሮ  ተልከዋል:: ነገር ግን […]

Continue reading …
በሸዋ ሮቢት ከተማ ጎማ እየተቃጠለ ለሰአታት መንገድ ተዘግቶ ዋለ

የዛሬው መንገድ መዝጋትና ጎማ ማቃጠል ደግሞ ለየት ያለ ነበር፡፡ ከስፍራው እንደደረሰን መረጃ በሰሜን ሸዋ ዞን የሸዋ ሮቢት ከተማ አንዲት ሴት በጩቤ ተወግታ ስትሞት አብሯት የነበረው ህፃን ልጇ ደግሞ በመታፈን ህይወቷ አልፎ ይገኛል፡፡ ሁለቱ ሰዎች በተገደሉበት ቤት ውስጥ ታፍኖ የነበረ ሌላ ህጻን ልጅ ወደ ህክምና ተወስዶ በተደረገለት እገዛ በጥሩ ጤንነት ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡  ይህን ድርጊት በመፈፀመም […]

Continue reading …
ኦዴፓ ለሕወሓት  ክስ ምላሽ ሰጠ – ፌደራል ስርዓቱ ይፈርሳል የሚባለው የኦሮሞን ሕዝብ ለማደናበርና ለማጋጨት ያለመ ነው ብሏል

ህወሓት የተመሰረተበትን 44ኛ ዓመት በማስመልከት ባወጣው መግለጫው በአሁኑ ሰዓት በትግላችን ያረጋገጥነውን ህገመንግስትና ፌደራላዊ ስርዓት ለማፍረስ የውስጥ የትምክህት ሀይልና ጸረ ልማታችን የሆኑ የውጭ ሀይሎች አንድ ላይ በመቀናጀት ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡ በመሰረቱ ይህ ሀላፊነት የጎደለው ተግባር ሀገራችንን ወደ ከባድ መተላለቅና መፈራረስ ሊያስገባት የሚችል አደገኛ አካሄድ መሆኑን ተረድታችሁ መላው ብሄሮች፣ ብሄረሰቦችና ህዝቦች በጋራ ትግል ሀገራችንና ህገ መንግስታችን […]

Continue reading …