Home » Archives by category » News Feature (Page 3)
ቴዎድሮስ ካሳሁንየአዲስ አበባ ሚሊኒዬም አዳራሽ ያቀረበው የሙዚቃ ትርዒት በዲቪዲ ተዘጋጅቶ የፊታችን ቅዳሜ ለሕዝብ እንደሚደርስ ታወቀ

ዝነኛው ድምፃዊ፣ የዜማና ግጥም ደራሲው ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) ጥቅምት 14 ቀን 2011 ዓ/ም 25 ሺህ ሕዝብ በታደመመበትና በታሪካዊው የአዲስ አበባ ሚሊኒዬም አዳራሽ ያቀረበው የሙዚቃ ትርዒት በዲቪዲ ተዘጋጅቶ የፊታችን ቅዳሜ ለሕዝብ እንደሚደርስ ታወቀ:: ይህ ሲዲ ለገና በዓል ሊቀርብ የነበረ ቢሆንም በአርቲስት ጎሳዬ ተስፋዬ ጥያቄ መሰረት መራዘሙን ዘ-ሐበሻ ቀደም ሲል መዘገቡ ይታወሳል:: ቴዲ ከ16 ዓመታት የሙያ […]

Continue reading …
ሕዝብ እንዲሰማህ ሰፊ አፍ ይኑርህ!

በላይነህ አባተ (abatebelai@yahoo.com) እንደሚታወቀው ለመስማት ተናጋሪና ሰሚ ያስፈልጋል፡፡ በተለይ ተመራምሮና መጻሕፍት አገላብጦ ሳይሆን ተባራሪ ዜናና አሉቧልታ በጀሮው ከጣራ እንደተቸከለ አንቴና እየቃረመ ያወቀ ለሚመስለው መንጋ ለመስማት እንደ ዲሽ የተንከረፈፈ ጆሮ ለመናገርም እንደ ሰማይ የተከፈተ አፍ ያስፈጋል፡፡ የፊደል ቆጣሪ ማይም እንደ ዝናብ አብራ በፈላባት ኢትዮጵያ ቀርቶ ፈላስፋዎችና ተመራማሪዎች በሞሉበት አሜሪካና አውሮፓም ሰፊ አፍ ዘወትር ያሸንፋል፡፡ ዓለም ከተፈጠረች […]

Continue reading …
ከኢሕአዴግ ፌዴራሊዝም ወደ መደመር ፌዴራሊዝም እንሻገር | ዶ/ር ዘላለም እሸቴ

የኢሕአዴግ ፌዴራሊዝም በብሔር ወይም በቋንቋ ላይ የተመሰረተ ነው እንዳልል ሁሉንም የኢትዮጵያ ብሔሮች ሆኑ ሁሉንም የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ማካተት ቀርቶ ባብዛኛው እንኳን የማያሳትፍ ስለሆነ በተለምዶ የዘር (ethnic) ፌዴራሊዝም የሚባለውን አጠራር መጠቀም አልችልም። አሁን ያለው ፌዴራሊዝምን “የኢህአዴግ ፌዴራሊዝም ” ከማለት በቀር ሌላ ቃል ላገኝለት አልቻልኩም። በዚያው መልክ ወደፊት እንዲኖረን የምሞግተው ፌዴራሊዝም በዓይነቱ አዲስ መሆን ያለበት ስለሆነ “የመደመር ፌዴራሊዝም […]

Continue reading …
‹‹7 ሚሊዮን ካድሬ መጅገሮች ሳይነቀሉ የኢኮኖሚ ለውጥ አይመጣም!!!››

ኢት-ኢኮኖሚ /ET- ECONOMY ‹‹7 ሚሊዮን ካድሬ መጅገሮች ሳይነቀሉ የኢኮኖሚ ለውጥ አይመጣም!!!››            ለቪዥን ኢትዮጵያ ሀገር ወዳድ ምሁራን የተበረከተ    ሚሊዮን ዘአማኑኤል  ህብለ ሰረሰር በሌላቸው ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የኦዴፓ/ኢህአዴግ ተከቦል፣ የተጠመጠሙበት የፖለቲካ ፓርቲዎ አንዳችም የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የማህበራዊ ጉዳይ ፍኖተ ካርታ ማቅረብ እስካሁን አልቻሉም፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በገንዘብ ማሰባሰብ ሥራ […]

Continue reading …
ሳሙኤል ተፈራ ለ22 ዓመታት ተይዞ የቆየውን  የ1,500 ሜትር  የቤት ውስጥ ሪኮርድ ሰበረ

እንግሊዝ በርኒንግሃም ውስጥ በተደረገው ሩጫ ውድድር አትሌት ሳሙኤል ተፈራ ለ22 ዓመታት ተይዞ የቆየውን  የ1,500 ሜትር  የቤት ውስጥ ሪኮርድ ሰበረ:: በሌላ በኩል አትሌት አልማዝ ሳሙኤል በ3,000 ሜትር ተወዳድራ በጥሩ ሰዓት አንደኛ በመውጣቷ የ2019 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮን ለመሆን በቃች:: – ዛሬ በመቀሌ በተደረገው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ መቀሌ 70 እንደርታ ባህርዳር ከነማን 1ለ0 አሸንፏል::  

Continue reading …
አቶ አርከበ እቁባይ ለሕወሓት መልቀቂያ  አስገቡ እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሐሰት ነው

አቶ አርከበ እቁባይ ለሕወሓት መልቀቂያ  አስገቡ እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሐሰት መሆኑን ጋዜጠኛ እሊያስ መሰረት አስታወቀ:: ኤሊያስ በፌስቡክ ገጹ እንዳስታወቀው “”አቶ አርከበን ህወሀት ጋር ተለያይተዋል እየተባለ ነው። የዚህን መረጃ እውነትነት ሊያረጋግጡልኝ ይችላሉ?” ብዬ ለጠየቅኳቸው መልስ በኢሜይል በሰጡኝ መልስ “አመሰግናለሁ! ይህ ሀሰት ነው” ብለው መልሰውልኛል።” ብሏል:: 

Continue reading …
ሕወሓት የተመሰረተበትን 41ኛ ዓመት በዓል ለማክበር የወጡ የመቀሌ የሕወሓት ካድሬዎች “ጌታቸው አሰፋ ውስጤ ነው” የሚል መፈክር ይዘው በአደባባይ ወጥተዋል

ሕወሓት የተመሰረተበትን 41ኛ ዓመት በዓል ለማክበር የወጡ የመቀሌ የሕወሓት ካድሬዎች “ጌታቸው አሰፋ ውስጤ ነው” የሚል መፈክር ይዘው በአደባባይ ወጥተዋል:: የትግራይ ሕዝብ አንገቱን የሚደፋው ለጸሎት ብቻ ነው እና ሌሎችንም መፈክሮች የያዙት እነዚሁ የሕወሓት ካድሬዎች አበል ከ75 ብር እስከ 125 ብር እንደተከፈላቸው ታውቋል::

Continue reading …
ዶ/ር አብይ አህመድ እና ለማ መገርሳ ም ዕራብ ወለጋ ተገኙ

ኦሮሚያን እያስተዳደረ የሚገኘው ኦዴፓ ሊቀመበርና ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ እንዲሁም የኦዴፓ ምክትል ሊቀመንበርና የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ  ከምዕራብ ወለጋ ከማኅበረሰብ አባላት ጋር ተወያዩ። አብዛኛው የም ዕራብ ወለጋ አካባቢ በኦነግ ቁጥጥር ሥር ሆነው መቆየታቸው ይታወሳል:: ሁለቱ መሪዎች በምዕራብ ወለጋ የቄለም ወለጋ ዞን አዋሳኝ ከሆነችው ቤጊ ወረዳ የማህበረሰብ አባላት ጋር በዛሬው ዕለት ሲወያዩ የአካባቢው […]

Continue reading …
በጎንደር ኮማንድ ፖስት ተቋቋመ | መከላከያ ገባ 

በምዕራብ እና በማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች የተከሰተውን ግጭት ለማርገብ የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ለፌዴራል መንግሥቱ ጥያቄ ማቅረቡ ታወቀ፡፡ በዚህ መሰረት የመከላከያ ሠራዊቱ የአካባቢውን ሠላም ለማስከበር ከዛሬ ጀምሮ ተሰማርቷል፡፡ በፀጥታ ኃይሉ አስተማማኝ ሰላም እስኪገኝ ድረስ በአካባቢው የተከለከለከሉ ተግባራትም ዛሬ ይፋ ተደርገዋል፡፡ በዚህም መሠረት ከጎንደር-መተማ መስመር ከመንገድ 5 ኪ.ሜ ክልል በቡድንም ይሁን በግል ትጥቅ ይዞ መንቀሳቀስ አይቻልም፤ በሁመራ […]

Continue reading …
በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በዛሬው እለት አንድ አስገራሚ የሰርግ ስነስርአት ተከናውኗል

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በዛሬው እለት አንድ አስገራሚ የሰርግ ስነስርአት ተከናውኗል፡፡ ሙሽራው አንተነህ አፖሎ የሚባል ሲሆን ለ14 አመታት በእስር ቤቱ የቆየ ታራሚ ነው፡፡ ሙሽሪት መስከረም ደገፉ ከዛሬው ባለቤቷ ጋር የተዋወቀችው እዚያው እስር ቤት የዛሬ ስምንት አመት ሰው ልትጠይቅ በሄደችበት ወቅት ነበር፡፡ ስምንት አመት ሙሉ በአይን ፍቅር የቆየው ግንኙነት ዛሬ ለየት ባለ ሰርግ ወደትዳር አምርቷል፡፡ በሰርጉ ስነስርአት […]

Continue reading …
ልእልት ሳራ ግዛው በ90 አመታቸው አረፉ

የግርማዊ ዐፄ ኃይለሥላሴ ልጅ የልዑል መኮንን ኃይለ ሥላሴ ባለቤት የሆኑት ልዕልት ሳራ ግዛው በ90 አመታቸው ማረፋቸው ተሰማ፡፡ ልእልቲቷ የንጉሡን አመራር የሚቃወሙ የኢትዮጵያ ወጣት ተማሪዎች ንቅናቄ አመራር ከነበሩት አንዱ የነበረውና አፍንጮ በር አካባቢ የተገደለው የጥላሁን ግዛው ታላቅ እህት ናቸው፡፡   በ1920 ዓም በአዲስ አበባ ከተማ የተወለዱት እኚህ ልዕልት እቴጌ መነን ካለፉ በኋላ በእሳቸው ምትክ የንጉሱ ልዩ […]

Continue reading …
አርበኞች ግንቦት 7 በደብረማርቆስ ሕዝባዊ ስብሰባ አደረገ

የአርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ መሪዎች ዛሬ በደብረማርቆስ ከተማ ከሚገኙ ደጋፊዎቻቸው ጋር ተወያዩ። የድርጅቱ አመራሮች ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እና አንዳርጋቸው ጽጌ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል:: አርበኞች ግንቦት 7 የዜግነት ፖለቲካ ብቸኛው ብሎም ሀገራችን ከገባችበት የዘርና የመከፋፈል አደጋ የምንወጣበት ስልት ነው ብሎ እንደሚያምን አመራሮቹ በስብሰባው ላይ ተናግረዋል:: –

Continue reading …
“ከኢትዮጵያዊነት አንሸሽም” – ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ – ክፍል ፩ | SBS Amharic

ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ፤ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ሊቀመንበር፤ ስለ ንቅናቄው ዓላማና ግቦች፣ የማንነት ፖለቲካና የወቅታዊውን የኢትዮጵያ ጉዳዮች አንስተው ይናገራሉ። – SBS Amharic

Continue reading …
ኤርሚያስ አመልጋ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በላኩት ደብዳቤ ዘመን ባንክን ቦይኮት አድርጉ ብለዋል (በቪዲዮ የቀረበ)

የአክሰስ ሪል እስቴት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ ኤርሚያስ አሜልጋ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን የበላይ አመራሮች ጋር በጥቅም በመተሳሰር የቀድሞውን ኢምፔሪያል ሆቴል ያለምንም የጨረታ ሂደት በ75 ሚሊየን ብር ውል ስምምነት በማሰር ሽያጭ እንዲፈፀም በማድረእግ የድርጅቱ ወቅታዊ ዋጋ 51 ሚሊየን ብር መሆኑ እየታወቀ በተጋነነ ዋጋ እንዲሸጥ በማድረግ በመንግስት ሀብት ላይ ከ24 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት አድርሰዋል […]

Continue reading …
አቶ ኤርሚያስ ከቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ለኢትዮጵያ ሕዝብ የላኩት  ደብዳቤ

የካቲት 7 ቀን 2011 ዓ.ም/ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት/ አ/አ ከ20 አመታት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ ወደ አገር ቤት ተመልሼ በተለያዩ የኢንቨስትመንት መስኮች ላይ ስስራ እንደመቆየቴ፣ የስራዬ ባህሪ ከባንኮች ጋር ያገናኘኝ ነበርና አዘውትሬ ወደተለያዩ የአገሪቱ ባንኮች እሄድ ነበር፡፡ ሁሉም ባንኮች ግን፣ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን የማይጠቀምና የደንበኞችን ፍላጐት በተቀላጠፈ መልኩ የማያረካ ኋላቀር የባንክ አሰራር ይዘው ነበር የማገኛቸው፡፡ በ2001 ዓ/ም […]

Continue reading …
ሁለት የራያ ተወላጅ ዲፕሎማቶች ሕወሓትን ለቀቁ

ሁለት የራያ ተወላጅ ዲፕሎማቶች ሕወሓትን ለቀቁ:: ሌሎችም እየተከተሉ ነው:: በራያ ሕዝብ ላይ ሕወሓት እየፈጸመ ያለውን ግፍ በማውገዝ፣ የራያ ማንነት እንዲከበር ሕዝቡ እየጠየቀ ያለው ጥያቄ እንዲመለስ የሚደግፉ፣ በፓርቲው ውስጥ የራያ ተወላጆች መገፋትና አለመታመንን የተቃወሙ ሁለት የራያ ተወላጅ ዲፕሎማቶች ሕወሓትን መልቀቃቸው ታወቀ:: በሳዑዲ አረቢያ በዲፕሎማትነት እያገለገለ የሚገኘው ሚስባህ ማህመድ እና በካይሮ በዲፕሎማትነት እያገለገለ የሚገኘው አሊ መሀመድ ሕወሓትን […]

Continue reading …
ጌትሽ ማሞ በሚኒሶታ  አስገራሚ ብቃቱን መድረክ ላይ  ያሳየበት ሙዚቃ – ‘የጠላሽ ይጠላ”

ጌትሽ ማሞ በሚኒሶታ አስገራሚ ብቃቱን መድረክ ላይ ያሳየበት ሙዚቃ – ‘የጠላሽ ይጠላ”

Continue reading …
የትግራይ ልዩ ሃይል መካከል 29 የልዩ ሃይል አባላት ለመጥፋት በዝግጅት ላይ እያሉ ተይዘው በወታደራዊ እስር ቤት ገቡ

በራያ ወረዳዎች እና አካባቢው ከተሰማሩት በሺ የሚቆጠሩ የትግራይ ልዩ ሃይል መካከል 29 የልዩ ሃይል አባላት; ለመጥፋት በዝግጅት ላይ እያሉ ተይዘው በወታደራዊ እስር ቤት መግባታቸውን የራያ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አመራር አቶ ደጀኔ አሰፋ ገለጸ::  እንደ አቶ ደጀኔ ገለጻ  እነዚህ ሊያመልጡ ሲሉ የተያዙት የልዩ ኃይል ወታደሮች ሕወሓት በራያ ሕዝብ ላይ እየወሰደ ያለውን እርምጃ በመቃወም ከህዝቡ ጋር መጣላት […]

Continue reading …
በነአብዲ ኢሌ የክስ መዝገብ ላይ የምስክሮች ማንነት ለተከሳሶች እንዳይገለጽ ተፈቀደ

ባለፈው ሳምንት ፍርድ ቤት ቀርበው የቀረበብኝ ክስ ድራማና ውሸት ነው ያሉት አብዲ ኢሌ ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረብይ:: በዛሬው የችሎት ውሎ ፍርድ ቤቱ ዐቃቤ ህግ በሶማሌ ክልል የቀድሞ ርእሰ መስተዳድር  አብዲ መሀመድ የክስ መዝገብ ላይ የምስክሮች ማንነት ለተከሳሶች እንዳይገለጽ ያቀረበውን አቤቱታ ተቀበለ። ክስ ከተመሰረተባቸው 47 ግለሰቦች ውስጥ ፍርድ ቤት ቀርበው ክሳቸው የተነበበላቸው አቶ አብዲ መሀመድ ዑመር፣ […]

Continue reading …
የሕዝብና ቤት ቆጠራ የሚያከናውኑ ሰዎች ቆጠራ ከመጀመራቸው በፊት ሊምሉ ነው

መንግስት አሁን ቆጠራውን ከሚያደርግ ሃገር በማረጋጋት ሥራ ላይ ቢጠመድ ይሻለዋል – የቆጠራውን ውጤት ተከትሎ ሊከሰት ለሚችል ግጭት አልተዘጋጀም እየተባለ አስተያየት በሚሰጥበት በዚህ ሰዓት  ከመጋቢት 29 እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ በሚካሄደው አራተኛው የህዝብና ቤት ቆጠራው ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ወደ ሥራው ከመግባታቸው በፊት ቃለ መሃላ እንደሚፈፅሙ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ ገለፀ፡፡ ቆጠራውን በተመለከተ በቂ ዝግጅት […]

Continue reading …